Tech & Science View All


አቅራቢ


...

የሚሞሉት የሞባይል ካርድ በኢንተርኔት አገልግሎት ምክንያት በፍጥነት እያለቀ ተቸግረዎል?
➤የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎቶ ሞባይል ካርድዎን እንዳይበለዉ ምን ማድረግ ይችላሉ?
➤በታሪፍ አንጻር 2G እና 3G ኔትወርኮች ተመሳሳይ ቢሆኑም የሚወስዱት የዳታ መጠን ግን በፍጹም አይገናኝም ስለሆነም አገልግሎትዎ 3G ከሆነ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅቦታል፡፡
ይህንን በአማርኛ የቀረበ ጠቃሚ መረጃ ያንብቡ፡፡
የሚሞሉት የሞባይል ካርድ በኢንተርኔት አገልግሎት ምክንያት በፍጥነት እያለቀ ተቸግረዎል?
ለሞባይል ካርድ የሚያወጡት ወጪ የተጋነነ ደረጃ ላይ ደርሶ “ብር እና ሀብትዎን” ይጎዳዎል ተብሎ ባይታሰብም፣ለከፈሉት ገንዘብ ግን ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት ማግኘት እንዳለቦት ሁላችንንም ያስማማናል፡፡
የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎቶ ሞባይል ካርድዎን እንዳይበለዉ ምን ማድረግ ይችላሉ?
1) የዳታ ኮኔክሽኑን መገደብ፡ ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ወቅት የሞባይል ዳታ ኮኔክሽኑን ማጥፋት የሞባይል ስልክዎ ያለ እርስዎ ፍቃድ የሚደርጋቸዉን የአፕሊኬሽን፣የኢሜይል ሲንኪንግ እና ሌሎች ካርድዎን ሊጠቀሙ የሚችሉ የኢንተርኔት እንቅስቃሴዎችን እንዲቀንሱ ይረዳዎታል፡፡
2) በራሳቸዉ አፕዴት የሚያደርጉ አፕሊኬሽኖችን መቆጣጠር፡ የሞባይል ስልክዎ ላይ የተጫኑ አፕሊኬሽኖች አንዳንዶቹ እርስዎ ባይፈቅዱም ኢንተርኔት ኮኔክሽኑን በመጠቀም በራሳቸዉ አፕዴት ያደርጋሉ፣ይህ ደግሞ የሞባይል ካርድዎን በመጠኑም ቢሆን ይበላዎል፡፡ስለዚህ የእንዚህን አፕሊኬሽኖች መቼት በራሳቸዉ አፕዴት እንዳያደርጉ ያስተካክሉ፡፡
3) ፌስቡክ(Facebook) አፕሊኬሽንን አይጠቀሙ፡ ፌስቡክ የሚጠቀሙ ከሆነ ኦፔራሚኒ(Opera Mini)፣ ክሮም(Chrome) ወይም ሌሎች መፈለጊያዎች(Browser
) ይጠቀሙ፡፡ የፌስቡክ(Facebook) አፕሊኬሽን ከፍተኛ ዳታ የሚወስድ እና የሞባይል ባትሪን የሚጨርስ እንደሆነ ይነገራል፡፡መፈለጊያዎች(Browser) መጠቀም አስቸጋሪ ከሆኖቦት ፌስቡክላይት(Facebook Lite) የሚባል አፕሊኬሽን ይጠቀሙ፣ይህ ከዋናዉ የፌስቡክ(Facebook) አፕሊኬሽን በተሻለ መልኩ ወጪ ይቆጥባል፡፡
4) ምስሎችን ወይም ቪዲዮዎችን አይስቀሉ(Upload)፣አ
ያዉርዱ(Download) እንዲሁም አይላላኩ፡
በስማርት ሞባይል ስልኮች የተቀረጸ የ 1 ደቂቃ ቪዲዬ እስከ 200 ሜጋ ባይት ሊደርስ ይችላል፣1 ፎቶ እስከ 40 ሜጋ ባይት ሊደርስ ይችላል፤ስለዚህም እንዚህን ቪዲዬዎችን እና ፎቶዎችን መስቀል(Upload)፣ማዉረድ (Download) እና መላላክ ሞባይል ካርድዎን በደንብ ይበላዎል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የኢንተርኔት አገልግሎትዎ 3G ከሆነ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅቦታል፤ በታሪፍ አንጻር 2G እና 3G ኔትወርኮች ተመሳሳይ ቢሆኑም የሚወስዱት የዳታ መጠን ግን በፍጹም አይገናኝም፡፡ በሀሳብ ደረጃ የ 2G እና 3G ኔትወርኮች የዳታ አጠቃቀም ተመሳሳይ ነዉ፣ነገር ግን አንድን የኢንተርኔት እንቅስቃሴ ለማከናወን 2G ኔትወርክ ረጅም ጊዜ ይፈጅበታል፡፡ ይህም እርስዎ 2G ኔትወርክ የሚጠቀሙ ከሆነ ከፍተኛ ዳታ የሚጠይቁ እና የሞባይል ካርድዎን የሚበሉ ቪዲዬዎች እንዳይጫወቱ፣ከተጫወቱም አነስተኛ በሆነ ዳታ እንዲተጫወቱም በማድረግ ወጪዎትን ይቀንሳል፡፡የ 3G ኔትወርክ ላይ ቪዲዬዎች ከፍተኛ ዳታን በሚጠይቁ የቪዲዬ ፎርማቶች እንዲታዩ የሚደረጉ ስለሆነ የሚወስደዉ የሞባይ ካርድም በዛዉ መጠን ይጨምራል፡፡
እስኪ በ 2G እና 3G የተወሰኑ ልዩነቶችን እንመልከት፡
1) ያለ እርስዎ ፈቃድ የሚደረጉ የኢንተርኔት እንቅስቃሴዎች፡ በ 2G ኔትወርክ የኢንተርኔት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ስለሆነ ያለ እርስዎ ፍቃድ የሚደረጉት የኢንተርኔት እንቅስቃሴዎች በቂ ኮኔክሽን ስለማያገኙ ዳዉንሎድ አያደርጉም፡፡ በ 3G ኔትወርክ የኢንተርኔት ፍጥነቱ ከፍተኛ ስለሆነ፣እርስዎ ባይፈቅዱም ዳዉንሎድ እና አፕሊኬሽን አፕዴት ያደርጋል፡፡
2) ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ጊዜ፡ መፈለጊያዎች(Browser) ሲጠቀሙ በ 2G ኔትወርክ እርስዎ እስከፈለጉት መረጃ ድረስ ብቻ ይከፍታል ከዛም ተጨማሪ ሲፈልጉ ቀጣዩን ይከፍትሎታል፡፡ በ 3G ኔትወርክ ላይ ግን አንድን ዌብሳይት ሲከፍቱ፤ለምሳሌ ፌስቡክ ሲከፍቱ ሁሉንም መረጃ፣ምስል እና ቪዲዬ ከፍቶ ይጠብቆታል፣እርስዎ ወዲያዉ አቋርጠዉ ቢወጡም እርስዎ ባላዩዎቸዉ ምስሎቹ እና ቪዲዬዎች የሞባይል ካርድዎ ይበላል፡፡
3) ቫይበር(Viber) እና ዋትስአፕ(Watsapp): በ 2G ኔትወርክ ምስሎች እና ቪዲዬዎች ወዲያዉኑ አይከፈቱም፡፡በ 3G ኔትወርክ ላይ ግን ምስሎች እና ቪዲዬዎች እርስዎ ባይፈልጉም ወዲያዉኑ ይከፈታሉ እናም የሞባይል ካርድዎን ይበላዋል፡፡
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶችን በመጠቀም አላስፈላጊ ከሆነ የሞባይል ካርድ ወጪ ይጠብቁ!

source: Ras Beki Beri kefet.com


Article read: 4387

On 07-05-2016

By Kefet Dtcom


Related articles


advertisment


utnaf ad
FOLLOW US ON THE NET


POPULAR VIDEOS View All

Click Here for Top Videos