Essay View All


~~~~እናቴ~~~


...

እናቴ አንድ አይን ብቻ ነው ያላት በዛም የመጣ
በጣም እጠላታለው::አባቴ...አባቴ ደግሞ የአራስ
ቤት ልጅ እያለው ነው የሞተው እሱ ከሞተ በኋላ
እኔና እናቴ በደሳሳ ጎጆዋችን ከድህነትጋ መኖር
ጀመርን::አባዬ ያስቀመጠው ገንዘብ ሲያልቅ
እናቴ በራችንጋ ትንሽዬ ሱቅ ከፍታ
መስራትጀመረች እማ ለኔ የማታደርግልኝ ነገር
የለም እኔ ግን በሷ አፍር ነበር ትዝ ይለኛል 5ኛ
ክፍል የወላጆች ቀን እናቴ ትምህርት ቤት አበባ
ይዛልኝ መጣች "እንዴት እንዲ ታደርገኛለች?
ማን ነይልኝ አላት?" ተሸማቀኩ በጥላቻ አይን
ገልምጫት እየሮጥኩ አዳራሹን ለቅቄ ወጣው::


በሚቀጥለው ቀን ት/ቤት ስመጣ ጓደኞቼ"እናቱ
1 አይን ነው ያላት"እያሉ ሲያወሩ ሰማዋቸው
በውስጤ ምናለ እናቴ ከዚች አለም ብጠፋ ብዬ
ተመኘው እቤት ስደርስም "ደስይበልሽ በጓደኞቼ
አሳቅሽብኝ....ቆይ እንድ አይንሽ የት ሄዶነው?
ሁሌ እንዲ ከምታሸማቂኝ ለምን አትሞቺም?"
ብዬ ጮህኩባት ምንም መልስ ሳትሰጠኝ
ወጣች::እንዲ ማለቴ ስሜቴን ቢኮረኩረኝም
ለረጅም ጊዜ ልላት ያሰብኩትን በማለቴውስጤን
ቀለል አለኝ
ብዙም ስሜትዋን የጎዳሁት አልመሰለኝምነበር
ያን ቀን ማታ ከእንቅሌፌ ተነስቼ ውሃ ልጠጣ
እቃ ቤትስገባ እናቴ እኔን ላለመቀስቀስ ቅስ ብላ
ስታለቅስ አገኘዋት ቅድም ባልኳት ነገር
እንደሆነ ገባኝ::


አሳዘነችኝ!
ድምፄን ሰምታ ቀና ስትል ካንዱ
አይንዋየሚወርዱ እንባዎቿን እየዋቸው::አይንዋ
በእንባ ተሞልቶ ሳየውይበልጥኑ ጠላኋት! በዛው
ቅፅበት ለራሴ እንድ ነገር ቃል ገባው አድጌ
ስኬታማ ስሆን እንድ አይናማዋን እናቴን ጥያት
እንደምሄድ!
ከዛን ቀን ጀምሮ ጠንክሬ መማር ጀመርኩ
እናቴን ትቻት ወደ ከተማ በመሄድ አለ በሚባል
ዩንቨርስቲ ውስጥ ስኮላርሺፕ አግኝቼ በነፃ
ትምህርቴን ተከታትዬ ጨረስኩ ጥሩ ስራ
ያዝኩ፤የራሴን ቪላ ገዛው ሚስት
አግብቼምልጆች ወለድኩ::

አሁን የተመኘሁትን
የልጅነት ህይወት እየኖርኩ እገኛለው::በጣም
ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ገንዘብ አለኝ፤ቆንጆ ቤት
አለኝ፤ደስተኛ ቤተሰብ አለኝ ከሁሉም በላይ ግን
የምጠላትን እናቴን የማላገኝበት ሩቅ ቦታ
ነውናየምኖረው ደስተኛ ነኝ:: አንድ ቀን ግን
ያላሰብኩት ዱብ እዳ መጣብኝ "ምን?!
ማነው ?!" እናቴ ነበረች ፀጉሮችዋ ሸብተው
ከስታና የተቀዳደዱ ቆሻሻ ልብሶች ለብሳ መጣች
ላምን አልቻልኩም ቤቴን እንዴት አወቀችው?!
ህፃንዋ ልጄ ፈርታት ሮጣ ወደቤት ገባች
እንዳላወቀ በመምሰል "ሴትዮ ምን ፈልገሽ
ነው?
የሰው ቤት ዝም ተብሎ እይገባም እሺ ውጪልኝ
ከቤቴ!!"አልኳት ኮስተር ብዬ እናቴ ደነገጠች "
ይቅርታ ጌታዬ አድራሻ ተሳስቼ ነው" ብላኝ
ወጣች.....ተመስገን አላወቀችኝም::ይህ ከሆን
ካንድ ወር በኋላ ለድሮ ት/ቤቴ የመዋጮ
ፕሮግራም ተዘጋጅቶ የት/ ቤቱ ዳይሬክተር
ደውለው ጠሩኝና ሄድኩ ፕሮግራሙ ሲያልቅ
በዛውም ያደኩበት ቤት ምን እንደሚመስል
ለማየት ስሄድ እናቴ መሬት ላይ ተዘርራ
አገኘዋት::ሞታለች!! ምንም
አላላቀስኩም::

እጇ ላይ ወረቀትአየውና አንስቼ
ማንበብ ጀመርኩ
ለኔ የፃፈችው ደብዳቤ ነበር...እንዲህ ይላል "ውድ
ልጄ,ካሁን በኋላ ሕይወት ማለትለኔ ምንም
አይደለችም::እንተ ወደምትኖርበት ከተማም
ተመልሼ አልመጣም::ልጄ ከምንም በላይ ግን
ናፍቆትህ ሊገድለኝ ነው ለምን አንድ አይን ብቻ
እንዳለኝ ጠይቀከኝ አልነገርኩክም ነበር
እውነታው ይህ ነው ልጄ.....ልጅ እያለክ ከባድ
የመኪና አደጋ ይደርስብክና አንድ አይንክ ይጠፋል
እንደማንኛውም እናት ያለ አንድ አይን ስታድግ
ማየት አልችልምና የኔን አይን አውጥተው ላንት
እንዲያረጉልህ ዶክተሮቹን ጠይቄ ፈቃደኛ ሆነው
አደረጉልህ.....
ለዚ ነው እንድ አይናማ የሆንኩብክ::እይዞህ ልጄ
ባደረካቸው ነገሮች ተቀይሜህ አላውቅም ነበር
ባለፈው እቤትክ መጥቼ የልጄን ልጅ በማየቴ
በጣም ተደስቻለው::ለወደፊትም በደስታ
እንደምትኖርም ተስፋ አደርጋለው::ልጄ እናትህ
በጣም ትወድሃለች"
.....አንብቤ ስጨርስ በሁለት እግሮቼ መቆም
አቃተኝ.እማ.....እማ........እማ እንባዬን እየዘራው
ምስኪኗን እናቴን አቅፌ ተንሰቀሰኩ ለኔ ብላ
ህይወትዋን የሰጠችውን እናቴን በራሴ እጅ
ገደልኳት...
ሞራል: እናት ማለት እውነተኛ ፍቅር ናት::
ክብር ይገባታል የሷን ብድር በምድር ላይ ማንም
በምንም ሊከፍለው አይችልምና ከመሞቷ በፊት
የሚገባትን ክብር እንስጣት::
እስታውስ:ሁላችንም አንድ እናት ነው ልትኖረን የምትችለው!

☞ውድ የፔጃችን ተከታታዮች የፌስቡክ ገፃችንን https://www.facebook.com/kefet.com ን ላይክ በማድረግ እንዲሁም የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ የተሻሉ እና ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ!


Article read: 7406

On 07-16-2016

By Kidus Michael


Related articles


advertisment


utnaf ad
FOLLOW US ON THE NET


POPULAR VIDEOS View All

Click Here for Top Videos