የአሜሪካ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅስቀሳ ወቅት ያሉትን ያደርጉ ይሆን?


...

የአሜሪካ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅስቀሳ ወቅት ያሉትን ያደርጉ ይሆን?

ትናንት በአሜሪካ በተደረገ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካኑን የወከሉት ዶናልድ ትራምፕ አሸንፈዋል።

እኝህ ተመራጭ ፕሬዚዳንት በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት አደርጋቸዋለሁ ያሏቸው በርካታ አወዛጋቢ ነገሮች ነበሩ።

ቢቢሲ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ቃላቸውን ጠብቀው አደርጋቸዋለሁ ያሏቸውን ካደረጉ ዓለም ላይ ተፅእኖን የሚፈጥሩ ናቸው ያላቸውን አምስት ጉዳዮች ዘርዝሯል።

ነፃ የንግድ ቀጠና

ዶናልድ ትራምፕ እከተለዋለሁ ያሉትን የንግድ ፖሊሲ በእርግጥም ከተገበሩ ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ዓለም ጋር የምታደርገውን የንግድ ልውውጥ በእጅጉን ይለወጣል።

ሰውየው በቅስቀሳቸው ወቅት አሜሪካ የፈረመቻቸውን የተለያዩ ነፃ የንግድ ስምምነቶችን ለመሰረዝ ዝተዋል። በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ መካከል የተፈረመው የሰሜን አሜሪካ ነፃ የንግድ ስምምነትም ከሚተቹት መካከል ይጠቀሳል።

እንደዚሁም ከዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሃገራቸውን እንደሚያስወጡ ተናግረዋል።

ከቻይና በሚገቡ ሸቀጦች ላይ የ45 በመቶ እና ከሜክሲኮ በሚመጡ ሸቀጦች ላይ ደግሞ 35 በመቶ ቀረጥ እጥላለሁም ብለዋል።

የዓየር ንብረት ለውጥ

ተመራጭ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስመረጥ ፓሪስ ላይ የዓለም ሃገራት ተሰብስበው ከረዥም ድርድር በኋላ የወለዱትን የፓሪስ የዓየር ንብረት ለውጥ ስምምነት እንደሚሰርዙ ዝተዋል።

ዋነኛ የከባቢ ዓየር በካይ የሆነች ሃገር ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ትራምፕ ይህን ካደረጉ ለፓሪሱ የዓየር ንብረት ለውጥ የከፋ ጉዳት ይሆናል።

ዩናይትድ ስቴትስ ለመንግስታቱ ድርጅት የዓየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራሞች የምታወጣውንም ወጪ እንደሚያቋርጡ ተናግረዋል።

ድንበር እዘጋለሁ

ዶናልድ ትራምፕ ቢመረጡ አሜሪካ ከሜክሲኮ ጋር የምትዋሰንበትን ድንበር በማሳጠር የሰዎች ፍልሰትን እንደሚያስቆሙ ተናግረዋል።

የአጥር ግንባታ ወጪውንም ሜክሲኮ ራሷ እንድትሸፍን አደርጋለሁም ብለዋል።

በተጨማሪም ወደኋላ ቢለሳለሱም 11 ሚሊየን ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከሃገር እንደሚያባርሩ፣ ሙስሊዎች ፈፅሞ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ አደርጋለሁም ብለው ነበር።

ኔቶ

ያለምንም ክፍያ ዩናይትድ ስቴትስ ለሌሎች ሃገራት ጥበቃ አትሰጥም የሚል አቋም ያላቸው ትራምፕ፥ በአውሮፓ እና እስያ የሚገኙ ሃገራት ለዩናትድ ስቴትስ በቂ ክፍያን እስካልፈፀሙ ድረስ ጥበቃ አታደርግም ይላሉ።

እንዲሁም ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ አባልነት ዋሽንግተንን ሊያስወጡ እንደሚችሉ ነው ተናግረው የነበረው።

ሩሲያ

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሃገራቸው ያላትን የሻከረ ግንኙነት ሊያለሰልሱ እንደሚችሉ እምነታቸውን ገልፀዋል።

ፑቲንን ጠንካራ መሪ የሚሉት ትራምፕ ከእርሳቸው ጋር ጥሩ ግንኙነት ቢኖራቸው እንደሚወዱ ነው በቅስቀሳቸው ወቅት የተናገሩት።


Article read: 2912

On 11-09-2016

By Kidus Michael


Related articles


advertismentFOLLOW US ON THE NET


POPULAR VIDEOS View All

 • Seifu on EBS: Musician Tadele Roba, His Wife and Seifu Friends Live Dance
  New
  • Share
  • |
  • 3338

  Seifu on EBS: Musician Tadele ...

 • Mogachoch EBS Latest Series Drama - S06E137 - Part 137
  New
  • Share
  • |
  • 2601

  Mogachoch EBS Latest Series Dr...

 • Jossy In The House: Interview With Mr. Lidetu Ayalew Part 2
  New
  • Share
  • |
  • 2589

  Jossy In The House: Interview ...

 • Mogachoch EBS Latest Series Drama - S06E139 - Part 139
  New
  • Share
  • |
  • 2471

  Mogachoch EBS Latest Series Dr...

 • Zemen Drama - Part 70
  New
  • Share
  • |
  • 2316

  Zemen Drama - Part 70...

 • Ethiopikalink Sheik Al Amudi Could be freed if he gave away 70% of his wealth Saudi off
  New
  • Share
  • |
  • 2191

  Ethiopikalink Sheik Al Amudi C...

 • Click Here for Top Videos